“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” "Come to me, all you who are weary and burdened, and I will give you rest." ማቴዎስ ፲፩፡፳፰ | Matthew 11:28
የመንፈሳዊ አገልግሎት እና እንክብካቤ Pastoral Care & Spiritual Support
እንኳን ደህና መጡ Welcome የደብረ ገነት ካቴድራል ቀሳውስት የማኅበረሰባችንን መንፈሳዊ ፍላጎት ለማገልገል ዝግጁ ናቸው። በደስታ፣ በህመም፣ በሀዘን ወይም በውዝግብ ጊዜ አባቶቻችን መመሪያን፣ ጸሎትን እና ሕይወት ሰጪ የቤተክርስቲያን ምስጢራትን ለመስጠት ዝግጁ ናቸው። The clergy of Debregenet Cathedral are here to serve the spiritual needs of our community. In times of joy, sickness, sorrow, or confusion, our priests are available to provide guidance, prayer, and the life-giving Holy Sacraments of the Church.
ጥሪያችን Our Calling
ጥሪያችን በሕይወትዎ ጉዞ ሁሉ ከእርስዎ ጋር አብሮ መጓዝ ነው። ሚስጥራዊ የሆነ መንፈሳዊ ድጋፍ እና ምክር እንሰጣለን፤ የታመሙትን እንጎበኛለን፤ ያዘኑትን እናጽናናለን፤ እንዲሁም አዲስ ሕይወትንና በክርስቶስ የሚመሰረቱ ትዳሮችን በደስታ እናከብራለን። Our calling is to walk with you through all of life's moments. We provide confidential spiritual support and counseling, visit the sick, comfort the grieving, and joyfully celebrate new life and new unions in Christ.
የመንፈሳዊ አገልግሎቶች Our Pastoral Services

ንሥሐ

Holy Confession

ቀሳውስት ለሚስጥራዊ የንሥሐ አገልግሎት ዝግጁ ናቸው። እባክዎን ቀጠሮ ለመያዝ ወደ ቢሮ ይደውሉ።

Priests are available for confidential confession (Penance). Please call the office to schedule a time.

የምስጢራተ ቤተክርስቲያን አገልግሎት

Sacramental Services

ለጥምቀት፣ ለጋብቻ፣ ለቀብር እና ለመታሰቢያ ጸሎቶች መመሪያ እና አፈጻጸም።

Guidance and officiating for Baptism (Christening), Marriage, Funerals, and Memorials.

የቤት በረከት

House Blessings

በቤትዎ እና በቤተሰብዎ ሕይወት ላይ የእግዚአብሔርን በረከት እና ሰላም መጥራት።

Invocation of God's blessing and peace upon your home and family life.

የሆስፒታል እና የቤት ጉብኝት

Hospital & Home Visits

ለታመሙ፣ ለአረጋውያን እና ከቤት መውጣት ለማይችሉ ጸሎት እና ቅዱስ ቁርባን ለማድረስ ዘወትር እንጎበኛለን።

Regular visits to the sick, elderly, and shut-ins to provide prayer and Holy Communion.

መንፈሳዊ ምክር

Spiritual Counseling

የሕይወት ፈተናዎች ወይም መንፈሳዊ ጥያቄዎች ለገጠሟቸው ግለሰቦች፣ ጥንዶች ወይም ቤተሰቦች የሚሰጥ ሚስጥራዊ ድጋፍ።

Confidential support for individuals, couples, or families facing life challenges or spiritual questions.

እንዴት እርዳታ መጠየቅ ይቻላል How to Request Care

ለአስቸኳይ ጊዜ | For Emergencies

እርስዎ ወይም የሚወዱት ሰው ሆስፒታል ከሆኑ ወይም አስቸኳይ የቄስ እርዳታ ካስፈለገዎት እባክዎን በዚህ ይደውሉ፡

If you or a loved one is in the hospital or facing an immediate life-threatening situation and requires a priest, please call:

204-123-4567

(ይህ የሕክምና ድንገተኛ አደጋ ከሆነ እባክዎን መጀመሪያ 911 ይደውሉ / If medical emergency, call 911 first.)

አስቸኳይ ላልሆኑ ጥያቄዎች | Non-Emergency Requests

ለጥምቀት፣ ለመታሰቢያ ጸሎት፣ ለጋብቻ ወይም ለቀብር ስነ-ስርዓት እባክዎን የቤተክርስቲያኑን ቢሮ ያነጋግሩ።

For scheduling Baptisms, Memorial Prayers, Weddings, or Funerals, please visit the church office or use the request forms below.