ለአንድ ዓመት ሙሉ የምግብ፣ የልብስና የመጓጓዣ ወጪዎችን ለመሸፈን ዋስትና መስጠት።
Providing full financial coverage for basic necessities including food and clothing for the first 12 months.
አዲስ መጤዎች ሲገቡ አስተማማኝና ምቹ የሆነ የመኖሪያ ቤት ማመቻቸትና ኪራይ መክፈል።
Securing and maintaining safe, permanent housing for the entire duration of the sponsorship period.
አዲስ መጤዎች በትምህርት፣ በጤና እና በሥራ መስክ እንዲሰማሩ ማገዝና ማበረታታት።
Facilitating emotional and social support, assisting with school enrollment, healthcare, and job searches.
ቤተክርስቲያናችን እንደ "Constituent Group" (CG) በመሆን ከስፖንሰርሺፕ ስምምነት ያዢዎች (SAH) ጋር በጥምረት ትሰራለች።
As a sponsoring congregation, we work under the umbrella of a Sponsorship Agreement Holder (SAH) to submit applications to Immigration, Refugees and Citizenship Canada (IRCC).
፩. ማመልከቻ (Application): በ SAH በኩል ማመልከቻዎችን ለካናዳ መንግስት እናቀርባለን።
፪. ዝግጅት (Preparation): ስደተኞቹ ከመምጣታቸው በፊት አስፈላጊውን የገንዘብና የቁሳቁስ ዝግጅት እናደርጋለን።
፫. አቀባበል (Arrival): በ ፲፪ ወራት ውስጥ ራሳቸውን እንዲችሉ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እናደርጋለን።